TM Law Firm Accessibility
×

ቋንቋ / Language: የቃለ-መጠይቁ ዋና ትንታኔ በአማርኛ ከዚህ በታች ቀርቧል። Click here for the English summary ↓

የማህበራችን መስራችና የታክስና የጉምሩክ ክፍል ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ፅዮን አድማሱ በቅርቡ ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፤ የኢትዮጵያ የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን ተቋማዊ እድገት፣ የቀን ተቀን የዳኝነት አሰጣጥ ሂደት፣ ያሉ ጠንካራ ጎኖች እና የቀጣይ ማሻሻያዎችን አስመልክቶ ሙያዊ ትንታኔ ሰጥተዋል። በዝግጅቱ ላይ ሌሎች የህግ ባለሙያዎች እና ተገልጋዮችም ተሳትፈው ተሞክሯቸውን አካፍለዋል።

በቃለ-መጠይቁ ወቅት ወ/ሮ ፅዮን አድማሱ በገቢዎችና ጉምሩክ መስሪያ ቤት ውስጥ ከነበራቸው የቀድሞ የስራ ልምድ እንዲሁም ላለፉት በርካታ ዓመታት በታክስ አማካሪነት እና በጠበቃነት በኮሚሽኑ ፊት ጉዳዮችን በመያዝ ካካበቱት ተሞክሮ በመነሳት፣ የታክስ ይግባኝ ሥርዓቱ በኢኮኖሚው እና በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና በዝርዝር አስረድተዋል።


በቃለ-መጠይቁ የተዳሰሱ ዋና ዋና ነጥቦች

  • የኮሚሽኑ ራሱን ችሎ በአዋጅ መቋቋም እና ነፃነት [00:01:23]፦ ቀደም ሲል የግብር ይግባኝ ሰሚ ጉባኤ በፍትህ ሚኒስቴር ስር አንድ ክፍል ሆኖ እና ከተለያዩ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በተውጣጡ ተደራቢ ዳኞች ይመራ እንደነበር አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ በታክስ አስተዳደር አዋጅ ራሱን የቻለ ተቋም ሆኖ ከተቋቋመ ወዲህ፣ የሙሉ ጊዜ ዳኞች እና የተደራጀ መዝገብ ቤት (ሬጅስትራር) በማግኘቱ በገለልተኝነት እና በነፃነት ጉዳዮችን ለማየት ትልቅ እመርታ ማሳየቱን ገልጸዋል።
  • የህግ እና የታክስ አካውንቲንግ (Tax Accounting) ጥምረት [00:08:12]፦ የታክስ እና የጉምሩክ ክርክሮች ተራ የህግ ጉዳዮች ብቻ ሳይሆኑ ጥልቅ የፋይናንስ እና የታክስ አካውንቲንግ እውቀትን የሚጠይቁ ናቸው። ኮሚሽኑ በነዚህ ሁለት መስኮች የሰለጠኑ ዳኞች ያሉት መሆኑ፣ የሂሳብ ስሌት ስህተቶችን እና ውስብስብ የታክስ ህግ ትርጉሞችን በብቃት ለመመርመር እንዳስቻለው አብራርተዋል።
  • የጉዳዮች አፈታት ፍጥነት እና የቀጠሮ መሻሻሎች [00:11:48]፦ ቀደም ሲል በአቤቱታ አቀራረብ፣ በመልስ፣ በመልስ-መልስ እና በቃል ክርክር ሂደቶች መካከል በርካታ ወራትን ይወስዱ የነበሩ ጉዳዮች፣ በአሁኑ ወቅት በአጭር ጊዜ እና በአንዳንድ መዝገቦች በሳምንታት ውስጥ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው እየተስተናገዱ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም ግብር ከፋዩም ሆነ መንግስት ገንዘባቸው ሳይታገድ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።
  • የኮሚሽኑ ጥምር ሚና፡ ይግባኝ ሰሚ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት [00:19:33]፦ ተቋሙ ስያሜው ይግባኝ ሰሚ ቢባልም፣ እንደ መደበኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቶች በህግ ነጥብ ላይ ብቻ ሳይሆን ፍሬ-ነገርን (Fact)፣ ኦዲት ሰነዶችን እና ማስረጃዎችን በቀጥታ ተቀብሎ የመመርመር እና የመመዘን ስልጣን ያለው በመሆኑ፣ በተግባር እንደ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት እና እንደ ይግባኝ ሰሚ አካል ሁለት ሚናዎችን አጣምሮ የሚሰራ መሆኑን ዳስሰዋል።
  • ለተከራካሪዎች የተሰጠ ሙያዊ ማሳሰቢያ [00:04:02]፦ የኮሚሽኑ ዳኝነት ውጤታማ የሚሆነው ተከራካሪ ወገኖች እና ጠበቆችም ራሳቸውን በሚገባ ሲያዘጋጁ ብቻ መሆኑን አስገንዝበዋል። ግብር ከፋዮችም ሆኑ አማካሪዎቻቸው ከጅምሩ በቅሬታ ደረጃ ጠንካራ ማስረጃዎችን በመያዝ፣ የተጣሱ የታክስና የጉምሩክ ህጎችን እንዲሁም የታክስ ሂሳብ ስህተቶችን በግልጽ እና ብቃት ባለው መንገድ ማቅረብ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በቀጣይ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ምክረ-ሃሳቦች

የወ/ሮ ፅዮን አድማሱ ዋና ዋና ምክረ-ሃሳቦች፡

  1. ልምድ ያላቸውን ዳኞች መመደብ [00:22:23]፦ በታክስ እና በጉምሩክ ጉዳዮች ላይ የካበተ ልምድ እና የሙያ ዳራ ያላቸውን ባለሙያዎች ወደ ዳኝነት ስርዓቱ ማምጣት እና መመደብ፤
  2. ተከታታይ እና ልዩ የሙያ ስልጠና መስጠት [00:10:52]፦ የታክስ፣ የጉምሩክ እና የሂሳብ አያያዝ ህጎች ባህሪያቸው ውስብስብ እና ሰፊ በመሆኑ፣ ለዳኞች በየጊዜው ተከታታይ የሆነ ልዩ የማብቂያ ስልጠናዎችን በመስጠት ሙያዊ ብቃታቸውን ይበልጥ ማጠናከር።

በቃለ-መጠይቁ ከተሳተፉ ሌሎች የህግ ባለሙያዎች የተነሱ ተጨማሪ ነጥቦች፡

  • የኮሚሽኑ ውሳኔዎች በገቢ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት በኩል የሚፈጸሙበትን ግልጽ የህግ ማዕቀፍ ማጠናከር [00:21:41]፤
  • ለህግ ተገማችነት እና ወጥነት ሲባል የቀድሞ ውሳኔዎችን መዝግቦ የማደራጀት (Case Indexing) ስርዓት መዘርጋት [00:22:46]፤
  • ከአዲስ አበባ ውጭ ላሉ ግብር ከፋዮች ተደራሽነትን ለማስፋት የክልል ቅርንጫፎችን መክፈት እና የዲጂታል (E-filing) አሰራርን ማጠናከር [00:23:44]፤
  • በክርክር ወቅት ተከራካሪ ጠበቆች የሌላኛውን ወገን ምስክሮች እና ኦዲተሮች የመስቀለኛ ጥያቄ (Cross-examination) የሚያቀርቡበትን አሰራር ግልጽ ማድረግ [00:24:06]።

English Summary

Our Founding Partner and Manager of Tax & Customs Department, W/ro Tsion Admassu, was recently featured in an interview on Fana Television discussing the institutional evolution, day-to-day adjudication, and procedural dynamics of Ethiopia’s Federal Tax Appeal Commission (የፌዴራል ታክስ ይግባኝ ኮሚሽን). The program also gathered perspectives from fellow legal practitioners and taxpayers appearing before the Commission.

Drawing on an extensive background within tax administration and years of direct advocacy before the Commission, W/ro Tsion shared practitioner insights on how specialized tax dispute forums foster fairness, commercial stability, and taxpayer confidence.


Key Interview Highlights

  • Autonomous Mandate & Independence [00:01:23]: Re-establishing the Commission as an autonomous body with full-time judicial benches marked a significant departure from its historical setup as a part-time board under the Ministry of Justice.
  • Intersection of Substantive Law & Tax Accounting [00:08:12]: Because tax and customs disputes require specialized financial analysis alongside statutory interpretation, having benches with specialized expertise in both disciplines is vital for properly evaluating audit assessments.
  • Procedural Speed & Case Management [00:11:48]: Notable procedural adjustments have shortened turnaround cycles that previously stretched over several months down to weekly calendars in many instances, preventing capital from being tied up unnecessarily.
  • Dual Mandate: Appellate Review & Trial of Fact [00:19:33]: The Commission operates both as an administrative appellate body reviewing tax authority decisions and as a first-instance forum directly examining records, evidence, and factual merits.
  • Litigant Preparation Standards [00:04:02]: Effective adjudication requires litigants and counsel to build solid factual records early and articulate statutory breaches and accounting errors clearly.

Recommendations for Continued Improvement

Recommendations Emphasized by W/ro Tsion Admassu:

  1. Recruiting Specialized Judicial Benches [00:22:23]: Appointing and assigning judges who possess strong background and hands-on experience in tax and customs disciplines;
  2. Continuous, Specialized Judicial Training [00:10:52]: Providing judges with ongoing, specialized training in tax legislation, customs rules, and tax accounting to continually sharpen their specialized adjudication capacity.

Additional Insights Raised by Fellow Legal Practitioners:

  • Clarifying statutory enforcement procedures for decisions rendered in favor of taxpayers against revenue collectors [00:21:41];
  • Instituting systematic case indexing of prior rulings to ensure legal predictability and uniformity across benches [00:22:46];
  • Expanding regional accessibility and accelerating e-filing systems for taxpayers based outside the capital [00:23:44];
  • Refining witness examination procedures to permit direct cross-examination of expert and auditor witnesses during hearings [00:24:06].